Abstract:
የሰቆጣ ቃል ኪዳን እ.ኤ.አ. በ 2030 የህፃናትን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት/መቀንጨርን/ ለማስቀረት በኢትዮጵያ
መንግስት ቁርጠኝነት የተዘጋጀ መረሃ ግብር ነው:: ሰቆጣ ቃልኪዳን ስርዓተ ምግብ ለኢኮኖሚ ልማት ያለውን መሰረታዊ
አስተዋፅኦ በመገንዘብ መንግሰት ለሰብዓዊ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠበት ነው፡፡ ይህም የሚተገበረው በሁለተኛው
ብሄራዊ የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም (NNP II) ስር ነው:: በቀጣይ የ15 ዓመታት መረሃ ግብር ይህ ፕሮገራም በአማራ እና
በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሚገኙና በተከዜ ተፋሰስ ከፍተኛ ተጽዕኖ በሚደርስባቸው 33 ወረዳዎች ይተገበራል::
ሁለተኛው የብሄራዊ ስርዓተ ምግብ እቅድ (NNP II) እና የሰቆጣ ቃልኪዳን መቀንጨርን ለመቀነስ የስርዓተ ምግብ ተኮር እና
አካቶ(Nutrition specific and sensitive) የተባሉትን የመተግበሪያ ስልቶችን ትኩረት በማድረግ ይንቀሳቀሳሉ:: እነዚሀ
ስልታዊ አላማዎች እና ተግባራትም ሊፈጸሙ የሚችሉት በሰቆጣ ቃል ኪዳን ወረዳዎች የባለድርሻ አካለት ቅንጅታዊ አሰራር ብቻ
ነው:: የባለድርሻ አካላት ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቀነስ የሚስችል ሲሆን የሰቆጣ ቃል ኪዳን
ዋና የትግበራ ዘዴም ነው ፡፡ቃል ኪዳኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ባለድርሻ አካላት ወደ ስራ ገብተዋል ፡፡
ከሰባት በላይ የመንግስት ሴክተሮች ፣ ለጋሽ ድርጅቶች ፣ ፈጻሚ አጋር አካላት (IPs) እና ሲቪል ማህበረሰብ (CSOs) በሃገር.፣
በክልል እና በወረዳ ደረጃዎች የሰቆጣ ቃል ኪዳን ባለድርሻ አካላት ናቸው :: ሆኖም የባለድርሻ አካላት ትብብር እና የአጋርነት
አስተዳደር ስርዓት (MSCPM) ቢኖርም በሰቆጣ ቃል ኪዳን መረሃ ግብር ላይ ትልቅ ክፍተት ነበር ፡፡