Abstract:
ይህ ሁለተኛው የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (ሁለተኛው ጤ.ዘ.ት.ዕ) ከ2013-2017 በጀት ዓመት መካከል ያለውን ጊዜ
የሚሸፍን ነው። ሁለተኛው ጤ.ዘ.ት.ዕ የአስር ዓመቱ የጤና ዘርፍ ዕቅድ የመጀመሪያ አካል ሆኖ ተሰናድቷል። ዕቅዱ በመጀመሪያው
ጤ.ዘ.ት.ዕ ጥልቅ ሁኔታዊ ትንተና እና የአፈፃፀም ግምገማ ላይ በመመርኮዝ የተዘጋጀ ሲሆን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ከግምት
ውስጥ ያስገባ እና ከአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ልማት ማዕቀፍ ጋር የተጣጣመ ነው።
በመጀመሪያው ጤ.ዘ.ት.ዕ ከ2008-2012 በጀት ዓመት ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ህዝብን ከመኖሪያቸው ያፈናቀሉ ውስጣዊ
ግጭቶች እና እንደ ኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ያሉ ችግሮች ቢኖሩም ጉልህ ስኬቶች ተመዝግበዋል።