Abstract:
የደም ማነስ በአለም ዙሪያ የሚታወቅ የህብረተሰብ የጤና ችግር ሲሆን ሁለት ቢሊዩን ህዝብ ተጠቂ ናቸው[1] ፡፡ በአለማችን 41.8% ነፍሰጡር እናቶችና 30.2% ነፍስጡር ያልሆኑ
እናቶች የደም ማነስ አለባቸው[1, 2]፡፡ ምንም እንኳን የተለያዩ የደም ማነስ በሽታ መንስኤዎች ቢኖሩም ከግማሽ በላይ የሚሆነው ግን በአይረን ንጥረ ነገር እጥረት ከሚከስት የደም ማነስ ጋር የተያያዘ ነው[2] ፡፡ የእናቶች የደም ማነስ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች በበርካታ ጥናቶች ዉስጥ ተገልፆአል [3]፡፡ እንደ አለም የጤና ድርጅት መረጃ 12.8% በእስያ እና 3.7%
የሚሆነዉበአፍሪካ አህጉር የእናቶች ሞት በቀጥታ ከደም ማነስ ጋር ይያያዛል [4]፡፡ ከዚህ ባሻገር የአይረን ንጥረ ነገር እጥረት 22% ለሚሆን የእናቶች ሞት በአለም አቀፍ ደረጃ
መሰረታዊ ምክንያት ነው [5]